25 ኢትዩጲያውያን ስደተኞች በየመን ባህር ሲጠፉ ከ20በላይ ህይወታቸው አልፏል፡፡

Written by on February 12, 2018

የካቲት 5 2010

25 ኢትዩጲያውያን ስደተኞች በየመን ባህር ሲጠፉ ከ20በላይ ህይወታቸው አልፏል፡፡
 
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት አይ-ኦ-ኤም አርብ እለት 25 ኢትዩጲያውያን በየመን ባህር ላይ መጥፋታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
የጠፉት ኢትዩጲያውያን በአራት መርከብ ተከፍለው ከተሳፈሩት እና በየመን ሻባዋ የተባለች የባህር ዳርቻ ላይ ከተገኙት 602 ወንዶች እና ሴቶች ስደተኛ ኢትዩጲያውያን ጋር አብረው የነበሩ ናቸው፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ጆኤል ሚልማን በጄኔቫ ለተባበሩት መንግስታት ባቀረቡት አጭር ማብራሪያ ላይ እንደተናገሩት ምን ያህል ኢትዩጲያውያን ጠፍተው ሊሆን እንደሚችል በትክክል ብዛታቸው ያልታወቀ ሲሆን በመርከብ ላይ ጉዟቸው ተገፍተው ወደ ባህር ሳይጣሉ አልቀሩም የተባሉት 22 ኢትዩጲያውያን አስከሬን ግን ተገኝቷል፡፡ ቃልአቀባዩ ከዚህ ባለፈ ስለክስተቱ ምንም የሰጡት ማብራሪያ ግን የለም፡፡
በተመድ ኢትዩጲያውያኑ ስደተኞች የተገኙበት አካባቢ የተልእኮ እና የአደጋ ጊዜ ዳይሬክተር የሆኑት ሞሀመድ አብዲከር በማህበረሰብ ገጽ ትዊተር ላይ በለጠፉት ጽሁፍ ላይ እንደገለጹት ስደተኞቹ ሀሙስ እለት ሌሊት ላይ ሲጓዙ ከነበረበት መርከብ ላይ ወርደው ወደ ባህር ዳርቻ እንዲዋኙ ተገደዋል፡፡ የመጡትም በሶማሊያ በኩል አድርገው ወደ የመን ሻባዋ ግዛት ነው ብለዋል፡፡ እስከእሁድ እለት ድረስ የ22 ኢትዩጲያውያን አስከሬን ሲገኝ ምን ያህል እንደጠፉ ግን አልታወቀም፡፡ የተቀሩት ጠፍተዋል የተባሉት ኢትዩጲያውያን አስከሬንም አልተገኘም፡፡
 
ባሳፍነው የፈረንጆቹ አመት 2017 በአብዛኛው በጅቡቲ በኩል በእቃ ወይም በሰው ማመላለሻ ጀልባ ወደ የመን የተሰደዱ 87ሺህ ስደተኞች ነበሩ፡፡
ከስደተኞቹ አብዛኞቹ በአረብ ሰላጤ ሀብታም ወደ ሚባሉት ሀገራት እንደተሰደዱም የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት አይ-ኦ-ኤም መረጃ ያሳያል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ኤጀንሲዎች በጦርነት እንዳልነበረች ወደሆነችው የመን እንደ ኢትዩጲያ እና ሶማሊያ ካሉ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዜጎች እንዳይሰደዱ በተለያዩ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]