አንድ የእንግሊዝ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፋብሪካ ሊገነባ ነው፡፡

Written by on February 12, 2018

አንድ የእንግሊዝ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፋብሪካ ሊገነባ ነው፡፡
የእንግሊዝ የጨርቃጨርቅ እና የግብርና ጥሬ እቃዎች አቅራቢ የሆነ ኢንትሬድ የተባለ ኩባንያ በኢትዩጲያ የአንድ መቶ ሚሊዩን የአሜሪካ ዶላር የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ፋብሪካ ሊገነባ ነው፡፡
ፍብሪካው በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገነባ ነው፡፡ መቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሀዋሳ እና ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ተከትሎ ባለፈው አመት የተመረቀ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲሆን በውስጡ የገቡትም ሆነ የሚገቡት ኩባንያዎች በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ምርት ላይ የሚሰሩ ናቸው፡፡
የእንግሊዝ ሀገሩ ኩባንያ ኢንትሬድ በሱዳን የጥጥ እርሻ አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከሱዳን መንግስት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረመ በኋላ ለ1ሺህ 300 የሀገሪቱ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል የተባለለት በጨርቃጨርቅ፤ እና አልባሳት እንዲሁም በመድሀኒት ማምረት ዘርፍ 200ሚሊዩን ዶላር ኢንቨስትመንት ለማድረግ ፈቃድ አግኝቷል፡፡
አሁን በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ፋብሪካውን ለመገንባት የእንግሊዙ ኩባንያ ዋና ሀላፊ ዋግዲ ማህጉብ ከኢትዩጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍጡም አረጋ ጋር መፈራረማቸው በኩባንያው ድረ ገጽ ላይ ሰፍሯል፡፡
አዲሱ ፋብሪካ የሀገሪቱን ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት አምራች እና ለውጪ ገበያ አቅራቢ ድርጅቶች ምርታቸውን ለማምረት ከውጪ ሀገራት ለመግዛት የሚያወጡትን ዶላር ለማስቀረት እና የሚያስፈልጋቸውን ጥሬ እቃ ከድርጅቱ መግኘት ያስችላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህ በመቀሉ ኢንዱስትሪ ፓርክ አዲስ ገቢ የሆነው ኩባንያ የፋብሪካውን ግንባታ በ16 ወራት እንዲጨርስ እቅድ ተይዞለታል፡፡
በሳለፍነው ህዳር ወር ላይ የቻይና ቁጥር አንድ ትልቅ የጨርቃጨርቅ ኩባንያ ውዢ የጥጥ አምራች ድርጅት በድሬዳዋ የተቀናጀ የጨርቃጨርቅ ዘርፍ ሰፊ እርሻ ለመስራት ከኢትዩጲያ መንግስት ጋር ተፈራርሞ ነበር፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]