የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት በሰሜን ኮሪያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበላቸው፡፡

Written by on February 12, 2018

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት በሰሜን ኮሪያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበላቸው፡፡

የአሜሪካ ባለስልጣናት ምክትል ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሙን ጄ በሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ታሪካዊ በሆነ መልኩ ጉብኝት እንዲያደርጉ ቅዳሜ እለት ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡ ይህ ከሆነ ከሰአታት በኋላ በደቡብ ኮሪያ እየተደረገ የነበረውን የክረምት ኦሎምፒክስ ሲመለከቱ የነበሩት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ከደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
የፕሬዚዳንት ሙን ቃልአቀባይ እንዳስታወቁት የኪም ጆንግ ኡንን የጉብኝት ጥያቄ አሁን የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ለመታደም ደቡብ ኮሪያ ያሉት የፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን እህት ኪም ዮ ጆንግ በሲኦል ቤተመንግስት ተገኝተው ነው ጥሪውን ለፕሬዚዳንቱ ያስተላለፉት፡፡
የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሙን ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ደቡብ እና ሰሜን ኮሪያ ስብሰባው ሊካሄድ የሚልበት ቦታ እና ሁኔታዎች ላይ በቀጣይ መወያየት እና አብረው መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ ሰሜን ኮሪያ እና አሜሪካም በአስፈላጊ ጉዳዩች ላይ በፍጥነት መወያየት እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል፡፡
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ በደቡብ ኮሪያ እየተካሄደ ባለው የክረምት ኦሎምፒክስ የመክፈቻ ስነስርአት ላይ በተገኙበት ወቅት ለሰሜን ኮሪያ ልኡካን ቡድን ከመቀመጫቸው አልተነሱም፡፡
ሲ-ቢ-ኤስ ኒውስ ዘግቦታል፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]