የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ ለአራት ተመራማሪዎች 11ሚሊዮን ዶላር ሊሸልም ነው ።

Written by on February 12, 2018

የካቲት 5  2010

የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ ለአራት ተመራማሪዎች 11ሚሊዮን ዶላር ሊሸልም ነው ።

አራቱ ተመራማሪዎች ለሽልማት የበቁት (genomics) ወይም የዘረመል ሳይንስን በመጠቀም አካባቢያችን እንዲሁም የአፍሪካዊያን ዘረመል የበሽታ ተጋላጭነት ላይ ያለውን ተፅእኖ በጥልቀት ለማጥናት ነው ።ሽልማቱ የሚሰጣቸው ከኢትዮጰያ፣ጋምቢያ፣ኡጋንዳና ደቡብ አፍሪካ የተገኙት ተሸላሚዎች H3AFRICA በተሰኘው ተቋም አማካኝነት የ4 አመት የምርምር ፕሮግራም እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል ።
የገንዘብ ሽልማቱ ለሚከተሉት ምርምሮች ድጋፍ ያደርጋል::
*የመስማት ችሎታን ማጣት የሚያስከትሉ ዘረመሎችን መለየት(ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ,ደቡብ አፍሪካ)
*በሰዎችና በወባ አምጪ ተህዋሲያን መካካል ያለው የዘረመል ልዩነት በበሽታው እድገት ላይ ያለውን ተፅእኖ ( ጋምቢያ)
*በተህዋሲያን እንዲሁም በሰዎች መካከል ያለው የዘረመል ልዪነት የሳምባ ነቀርሳ ወይም ቲቢ ተጠቂነት ላይ ያለውን ተፅእኖ መረዳትና አዳዲስ መድሀኒቶች እንዲሁም ክትባቶችን መፍጠር (ኢትዮጰያ)
*በተጨማሪም ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸው የቢልሃርዚያና የእንቅልፍ በሽታ የሚያጠቃቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች መለየት(ማኬሬሬ ዩኒቨርሲቲ, ኡጋንዳ) ናቸው፡፡
የዘረመል ጥናት እንደ ካንሰርና ስኳር የመሳሰሉ በሽታዎችን ይበልጥ ለመረዳትና አዳዲስ የህክምና ዘዴዎችን ለመፍጠር ያስችላል ።


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]