የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቡሩንዲ ስደተኞችን አስመልክቶ ያወጣው መረጃ ከ እውነት የራቀ ሲል የሀገሪቱ መንግስት አስተባበለ ፡

Written by on February 9, 2018

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቡሩንዲ ስደተኞችን አስመልክቶ ያወጣው መረጃ ከ እውነት የራቀ ሲል የሀገሪቱ መንግስት አስተባበለ ፡፡

የቡሩንዲ መንግስት እንዳስታወቀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሀገሪቱን ስደተኞች አስመልክቶ ያወጣው የቁጥር መረጃ ሆነ ተብሎ የተቀነባበረ እንደሆነ ገልጧል፡፡

የ ሀገር ውስጥ ጉዳዮች ተባባሪ ሚንስትር የሆኑት ናታርጃ ሲናገሩ የተባበሩት መንግስታት የ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ 430 ሺህ ብሩንዳዊያን እ.ኤ.አ በ 2015 ከ ሀገራቸው እንደወጡ አልተመለሱም ሲል ቢገልፅም ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ከ 2 መቶ ሺህ የሚበልጡ ዜጎች መኖራቸውን እውቅና መስጠት አለመፈለጉ ተገቢ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ተባባሪ ሚንስትሩ ይህን ይበሉ እንጂ የተቋሙ መረጃ እንደሚያስረዳው በ ሀገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ተከትሎ የተፈጠረውን ሰብኣዊ ቀውስ በመፍራት በዚህ አመት ብቻም ከ50 ሺህ የሚበልጡ ቡሩንዳውያን ሀገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡

ዘገባው የ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ነው::


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]