በኬንያ 2 ታዋቂ የምሽት ጭፈራ ቤቶች ተዘጉ::

Written by on February 9, 2018

በኬንያ 2 ታዋቂ የምሽት ጭፈራ ቤቶች ተዘጉ::

በኬንያ ናይሮቢ የሚገኙ ሁለት ታዋቂ የምሽት ጭፈራ ቤቶች የተዘጉ ሲሆን የምሽት ቤቶቹ ባለቤቶችና ደንበኞች ግን ተቃዉሞ እያሰሙ ይገኛሉ፡፡

የምሽት ቤቶቹ ሊዘጉ የቻሉት በእንቅልፍ ሰአት የሚረብሹ ድምጾች ስላላቸዉና የስርቆት ወንጀል በምሽት ቤቶቹ እየተንሰራፋ በመምጣቱ በመሆኑ እንደሆነ የሀገሪቱ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታዉቋል፡፡

የምሽት ጭፈራ ቤቶቹ ባለቤቶችና ተገልጋዮች ግን ይህ ድርጊት አያስማማንም ሲሉ አደባባይ ወጥተዋል፡፡

በሰልፉ ላይ የተገኙ የሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸዉ ይህ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ ይገባዋል ሲሉ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል፡፡

በናይሮቢ ከሁለት ሳምንት ቀደም ብሎ በምሽት ጭፈራ ቤት በተፈጠረ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ያስታወሰዉ የናይሮቢ ፖሊስ እርምጃዉ ተገቢ ነዉ ሲል ተደምጧል፡፡

ዘገባው የኦልአፍሪካን ነው፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]