በኬንያ እንዲዘጉ የታገዱት የግልና የመንግስት ሬዲዮ ጣቢያ ሀላፊዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው፡፡

Written by on February 9, 2018

በኬንያ እንዲዘጉ የታገዱት የግልና የመንግስት ሬዲዮ ጣቢያ ሀላፊዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው፡፡

በኬንያ የራይላ ኦዲንጋን ቃለመሃላ ዘግባችኋል የተባለ የግልና የመንግስት ሬዲዮ ጣቢያዎች ጣቢያቸውን እንዲዘጉ እገዳ እየተጣለባቸው ነው፡፡

የሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን ባለስልጣን እንደገለፀው ራይላ ኦዲንጋ በቃለመሃላቸው ወቅት የተናገሩት ንግግር አግባብ እንዳልሆነ እያወቁ በሀገሪቱ የሚገኙ ቁጥራቸው ያልታወቀ የግልና የመንግስት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጉዳዩን ዘግበዋል ሲል ተናግሯል፡፡

በዚህም የተነሳ እነዚህ ጣቢያዎች እንዲዘጉ የተደረገ ሲሆን የነዚህ ጣቢያዎች ሃላፊዎች ግን አግባብ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ይህ እገዳ ሊነሳልን ይገባል አለበለዚያ ግን ሰልፍ እንወጣለን ሲሉም ሃላፊዎቹ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡
የሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ግን ቅጣቱ ተገቢና አግባብ ያለው ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]