በአለም አቀፍ የአውሮፕላን አምራች ድርጅቶች ዋና ተቀናቃኝ የሆኑት ቦምባርዲር እና ኤር ባስ የቦምባርዲር ሲ ሲሪየስ የተባሉ የአውሮፕላን ምርቶች ላይ በጋራ ሊሰሩ ነው፡፡

Written by on October 22, 2017

በአለም አቀፍ የአውሮፕላን አምራች ድርጅቶች ዋና ተቀናቃኝ የሆኑት ቦምባርዲር እና ኤር ባስ የቦምባርዲር ሲ ሲሪየስ የተባሉ የአውሮፕላን ምርቶች ላይ በጋራ ሊሰሩ ነው፡፡
የአውሮፓው አውሮፕላን አምራች ድርጅት ኤር ባስ በቦምባርዲር ሲ ሲሪየስ የአውሮፕላን አይነቶች ምርት ላይ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚወስድ ተናግሯል፡፡

ቦምባርዲር በእነዚህ አይነት አውሮፕላኖቹ ምርት በኩል ከፍተኛ ችግር እያጋጠመው ያለ ሲሆን በቅርብ ጊዜም አሜሪካ 300 በመቶ የሚሆን ወደ ሀገሪቱ የሚያስገባቸው ምርቶች ላይ የሚከፍለው ቀረጥ ጥላበታለች፡፡
የቦምባርዲር ሰሜናዊ አየርላንድ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ማይክል ራየን ስምምነቱ በጣም ጥሩ ዜና ነው ብለውታል፡፡
የዚህን አውሮፕላን አምራች ድርጀት ሲ ሲሪየስ የተባሉ የአውሮፕላን ምርቶች ለመገንባት በፋብሪካው አንድ ሺህ ሰራተኞች ይሰራሉ፡፡
ኤርባስ የሚሳተፍባቸው የእነዚህ አውሮፕላኖች ግንባታ ላይ የ50 ነጥብ 01 ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ስምምነቱ በተጨማሪም ኤር ባስ ከቦምባርዲር የ ሲ ሲሪየስ አውሮፕላን ምርቶችን እስከ 2023 ድረስ የመግዛት ሙሉ መብት ሰጥቶታል፡፡ (ቢቢሲ ዘግቦታል)


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]