ከደረጃ ምደባ ጋር ተያይዞ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ እንደማይኖር እና ፍፁም ውሸት ነው ሲል የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

Written by on December 29, 2017

ከደረጃ ምደባ ጋር ተያይዞ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ እንደማይኖር እና ፍፁም ውሸት ነው ሲል የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

የስራ መደብ ትግበራ በአብዛኛው የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ሰራተኞች በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ይህ የስራ መደብ ትግበራ በተመሳሳይ የስራ መስክ ተመሳሳይ ክፍያ የሚል ሲሆን ከዚህ የስራ መደብ ትግበራ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ሰዎች የደሞዝ ጭማሪ ይኖራል የሚል እምነት አላቸው፡፡
ከዚህ የስራ መደብ ጋር ተያይዞ ምንም አይነት የደሞዝ ጭማሪ እንደማይኖር የኢ.ፌ.ድ.ሪ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃይል ልማት ሚኒሰቴር አስታውቋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በዚህ የስራ መደብ ትግበራ ጊዜ የደሞዝ ጭማሪ የሚኖራቸው ሊኖርም ላይኖርም ይችላል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
በማህበራዊ ትስስር ገጾችም የሚነበቡት ነገሮች የመንግስት ሰራተኞችን ግራ እያጋባ ይገኛል፡፡ ይህንንም ነገር የሚያደርጉ ሰዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ተገልጻል፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]