ሀገሪቱ ከገባችበት አለመረጋጋት ለመውጣት አርቆ አሳቢነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡

Written by on December 21, 2017

ሀገሪቱ ከገባችበት  አለመረጋጋት ለመውጣት አርቆ አሳቢነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጲያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂዎች በወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ በሰጡት ጋዜጣ መግለጫ  በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩትን አለመረጋጋቶች ለመፍታት አርቆ አሳቢነት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ በተለይም ከፍተኛ የትመህርት ተቃማት በሚገኙባቸው አካባቢዎች በአገሪቱ ልማትና እድገት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ወጣት ተማሪዎች ተጠቃሚ አልሆኑም ፡፡

የወጣቶቹን ተጠቃሚ አለመሆን ተከትሎና ከዚህ በፊት ሳይፈቱ በይደር በቆዩ ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት  በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ሰላምና አለመረጋጋት ባለመኖሩ  ጉባዬው መግለጫ መስጠቱ ግድ  ብሎታል ብሏል

የኢትዮጲያ አይማኖት ተቋማት ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል የሆኑት ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብረሃ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዳዲስ የምርምር ሀሳቦች የሚፈልቅባቸው፣የማህበረሰብ ችግሮችን በተግባራዊ ምርምሮችና ጥናቶች ሁነኛ መፍትሄ የሚሰጥባቸው ፣የሀሳብ ትግልና ድንበር ተሸጋሪ ጥልቅ ምሁራዊ አስተሳሰብ የሚቀረፅባቸው  ተቋም መሆን ሲገባቸው በስሜታዊነት የሚነዱ ጥልቅ አስተውሎት የማይታይባቸውን  ተቀባይነት የማያገኙና ለፀፀት የሚዳርጉ ውሳኔዎችን መወሰን እንደሌለባቸው ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ በከፍተኛ ተቋማት እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሉ ተማሪዎች ጠንካራ ሀገር እንዲኖራቸው ሊተጉ ፣የፌደራልና የክልል መንግስታት የስራ አላፊነታቸውን እንዲወጡ፣የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ አቋማቸውን ሳይስቱ በአገራዊ አጀንዳዎች ላይ ገንቢ አሳብ እንዲያቀርቡ ብዙአን መገናኛዎች ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህ/ሰቡ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]