እንቦጭ አረም ያደረሰውን ጉዳት የሚመረምር የጋዜጠኞች ቡድን ወደ ባህርዳር ሊጓዝ ነው፡፡

Written by on December 20, 2017

እንቦጭ አረም ያደረሰውን ጉዳት የሚመረምር የጋዜጠኞች ቡድን ወደ ባህርዳር ሊጓዝ ነው፡፡

ከተለመደው ሙያዊ ሃላፊነት ባለፈ ዜግነታዊ እና ሃገራዊ ግዴታውን ለመወጣት የተቋቋመው የኢትዮጲያ በጎ ፈቃደኛ ጋዜጠኞች ኔትወርክ ተቋቁሟል፡፡
ኔትወርኩ የጣና ሀይቅን በመውረር በሃይቁ ላይና ሃይቁ ውስጥ ኑሯቸውን ባደረጉ እንስሳት ላይ ያደረሰውን መጠነ ሰፊ ጉዳት ከስፍራው ላይ በመገኘት በችግሩ ዙሪያ ሰፊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ለማቀረብ ነው፡፡
የኔትወርኩ አስተባባሪ የሆኑት ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ እንደተናገሩት የእንቦጭ አረም በሃይቁ ላይ እያደረሰ ካለው ጥፋት በተጨማሪ በቢሾፍቱ ሃይቆችና በጋምቤላ አካባቢ አረሙ በመታየቱ ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከ30 እስከ 35 ጋዜጠኞች በሚሳተፉበት በዚሁ ጉዞ  ላይም  እንቦጭን በተመለከተ በባህርዳርና በጎንደር ከተሞች  ከባህርዳር ዩንቨርስቲ የአማራ ክልል የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቀ ባለስልጣን እና ምሁራን መረጃ ማጠናቀርና የፓናል ውይይቶች ይካሄዳል፡፡

እንቦጭ በአማዞን ተፋሰስ አካባቢ በተለይም በብራዚል አካባቢ መነሻውን በማድረግ  በዓለም ላይ የተባዛ አረም መሆኑን የአለም ምግብ ድርጅት እ.ኢ.አ 2002 በጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

የቤልጂየም ቅኝ ገዢዎች በረዋንዳ የነበራቸውን ይዞታቸውን ለማስዋብ በሚል ወደ አፍሪካ ይዘው መግባታቸውን ተከትሎ  በታችኛው የቪክቶሪያ አካባቢ ከ19 88 ጀምሮ ተስፋፍቷል፡፡

በዩኒስኮ የተመዘገበውና ከአገሪቱ ጨው  አልባ ውሃ ውስጥ ግማሹን የያዘው የጣና አይቅ ለመጀመሪያ ጊዜ የተወረረው እ.ኢ.አ በ2011 ሲሆን በወቅቱ 4ሺህ ኤክታር የሚሆነው የአይቁ ክፍል በአረም ተሸፍኖ ነበረ፡፡

የአማራ ክልል የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቀ ባለስልጣን አስተባባሪነት አይቁን የሸፈነውን አረም ለመንቀል ከ ጥቅምት 2011 እስከ ታህሳስ 2013 እ.ኢ.አ በተሰራ ስራ ከአስራ ስድስት ሚሊየን ሰዎች በላይ ቢሳተፉበትም ውጤታማ አልሆነም፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]