የአፍሪካ ልማት ባንክ የአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ መስመሮችን ለማሻሻል ከ101ሚሊዩን ዶላር በላይ ብድር እና እርዳታ ሰጠ፡፡

Written by on November 29, 2017

የአፍሪካ ልማት ባንክ የአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ መስመሮችን ለማሻሻል ከ101ሚሊዩን ዶላር በላይ ብድር እና እርዳታ ሰጠ፡፡

ልማት ባንኩ ገንዘቡን የፈቀደው በከተማዋ የኤሌክትሪክ ሀይል ክፍፍል ዙሪያ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 ያደረገውን ጥናት መሰረት አድርጎ ነው፡፡የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ መስመሮችን ለማሻሻል እና የኤሌክትሪክ ሀይል ክፍፍሉን የተሻለ ደረጃ የማድረግ ፕሮጀክቱ የሶስት አመት ቆይታ ይኖረዋል፡፡

በፕሮጀክቱ መሰረት 545 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ አዳዲስ የመካከለኛ ኤሌክትሪክ ሀይል ተሸካሚ መስመሮች ይገነባሉ፡፡582 ማከፋፈያ መስመሮችም ይዘረጋሉ፡፡ በተጨማሪም 14 ንኡስ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና የመቆጣጠር እና የሀይል ጥያቄዎችን እንዲያስተናግዱ ተደርገው ይሰራሉ፡፡ከእነዚህ ባለፈም በዚህ የሶስት አመት ፕሮጀክት ዘጠኝ በከተማዋ የሚገኙ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል መስመሮች የማሻሻል ስር ይሰራላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንዲሁም አንድ 132ኪሎ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ ሀይል የመሸከም አቅም ያለው እና ርዝመቱ 3.8 ኪሎ ሜትር የሆነ መስመርም ይዘረጋል፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]