በኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ በተነሳ ተቃውሞ ግንባታው የቆመው ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ ከይቅርታ በኋላ በድጋሚ ተጀምሯል፡፡

Written by on November 29, 2017

በኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ በተነሳ ተቃውሞ ግንባታው የቆመው ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ ከይቅርታ በኋላ በድጋሚ ተጀምሯል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎችም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ በቻይናው ሲ-ሲ-ሲ-ሲ ኩባንያ ሲገነባ የነበረው የአረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ በደረሰበት መጠነኛ ጉዳት ግንባታው ተቋርጦ ነበር፡፡
ለግንባታው መቋረጥ መነሻ የሆነውም በአካባቢው ነዋሪዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ነው፡፡ነዋሪዎቹ ተቃውሞውን የቀሰቀሱበት ምክንያት ደግሞ በአረርቲ ከተማ ለሁለት ሳምንት የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ መቆየቱ ነው፡፡በነዋሪዎቹ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ላይ ጉዳት በማስከተሉ ግንባታውን እንዲቆም ማድረጉን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር በላቸው መኩሪያ ለዛሚ ተናግረዋል፡፡
ባሳለፍነው ዓርብ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኩ ኃላፊዎች በተገኙበት፣ የአረርቲ ከተማ ነዋሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በተቃውሞው ስለደረሰው ጉዳት ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]