የትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሰባተኛ መገጣጠሚያ ማሻሻያ ስራዉን አስመረቀ፡

Written by on November 14, 2017

የትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሰባተኛ መገጣጠሚያ ማሻሻያ ስራዉን አስመረቀ፡፡
የብለንበርግ ግሎባል ሮድ ሴፊቲ ኢንሼቲቭ ከተባለዉ ግብረ ሰናይ ድርጅትና አጋር ድርጅት ከሆነዉ ናክቶ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የሚታየዉን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ፤ የመንገድ ተጠቃሚዉ የትራፊክ ስርዐትን እንዲከተል ማድረግ በከተማዋ መንገዶች ላይ ማሻሻያዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

ከነዚህም መንገዶች መካከል ብዙ እንቅስቃሴ የሚደርግበት የሰባተኛ አካባቢ የመንገድ መገጣጠሚያ ማሻሻያዉን አስመርቋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በጎዳና የትራፊክ አደጋ በአመት ከ1.3 ሚሉየን ህዝብ በላይ ሲሞት በአዲስ አበባ ብቻ 2016 ላይ ከ448 በላይ በትራፊክ አደጋ ሲሞቱ 1›912ቱ ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸዉ 1.201 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በመንገድ ላይ በሚደርስ አደጋ ህይወታቸዉን እንዳጡ የአዲስ አበባ ፖሉስ ኮሚሽን ሪፖርት ያመለክታል፡፡
የሰባተኛ መገጣጠሚያን ያስመረቀዉ የብለምበርግ አለማቀፍ የደህንነት ኢኒሼቲቭ ከትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር ሲሆን እ.እ.አ 2014 ሊይ በ12ሚሉን ዶላር በጀት በያዘዉ የአምስት አመት እቅድ አስር ከተሞችን የመገጣጠሚያ መንገድ ለመገንባት ያቀደ ሲሆን አዲስ አበባ አንዷ ነች፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]