በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የበርበሬ ዋጋ ጨምሯል ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለፁ፡፡ የሚመለከተው አካል በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥቶበታል፡፡

Written by on October 25, 2017

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የበርበሬ ዋጋ ጨምሯል ሲሉ ቅሬታቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ በፊት ይሸጥ የነበረው ከ 37 እስከ 40 ሲሆን አሁን ላይ ግን እስከ 62 ብር በኪሎ ተጠይቀናል ብለዋል፡፡

በመርካቶ፣ ሾላ እና አቃቂ ገበያዎች ተዘዋውረን በተመለከትንበት ወቅት በኪሎ እስከ 55 ብር ሲሸጥ የታዘብን ሲሆን፡፡

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው በንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ በዚህ ወቅት መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመው በቀጣዩ ወር እንደሚስተካከል አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ የተለያዩ ምክንያቶችን ተከተሎ በፍጆታ እቃዎች ላይ ከፍተኛ ዋጋ ማስከፈል የተለመደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

    


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]