ዜና

Page: 3

የአፍሪካ ልማት ባንክ የአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ መስመሮችን ለማሻሻል ከ101ሚሊዩን ዶላር በላይ ብድር እና እርዳታ ሰጠ፡፡ ልማት ባንኩ ገንዘቡን የፈቀደው በከተማዋ የኤሌክትሪክ ሀይል ክፍፍል ዙሪያ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 ያደረገውን ጥናት መሰረት አድርጎ ነው፡፡የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ መስመሮችን ለማሻሻል እና የኤሌክትሪክ ሀይል ክፍፍሉን የተሻለ ደረጃ የማድረግ ፕሮጀክቱ የሶስት አመት ቆይታ ይኖረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ መሰረት 545 […]

የኢትዮጲያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ከድርድሩ ራሱን አገለለ፡፡ይህን ያስታወቀው ለጣብያችን በላከው መግለጫ ነው፡፡ለዝርዝሩ ከስር ያለውን ኦዲዮ በመጫን ያዳምጡ፡፡

በኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ በተነሳ ተቃውሞ ግንባታው የቆመው ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ ከይቅርታ በኋላ በድጋሚ ተጀምሯል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ በቻይናው ሲ-ሲ-ሲ-ሲ ኩባንያ ሲገነባ የነበረው የአረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ በደረሰበት መጠነኛ ጉዳት ግንባታው ተቋርጦ ነበር፡፡ ለግንባታው መቋረጥ መነሻ የሆነውም በአካባቢው ነዋሪዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ነው፡፡ነዋሪዎቹ ተቃውሞውን የቀሰቀሱበት ምክንያት ደግሞ በአረርቲ ከተማ […]

የእንቦጭ አረም ማሽን በይፋ ተመርቆ የሙከራ ስራ ጀመረ፡፡ ለረዥም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው በዩኒቨርሲቲው የተሰራው ይህ ማሽን በትላንት እለት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሙከራ ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡ ማሽኑ በሰዓት 50 ኩንታል እንቦጭ አረም መሰብሰብ የሚችል ሲሆን የሰው ሀይልን ሳይጨምር እስካሁን 2.2 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበታል፡፡ ማሽኑን በይፋ መርቀው ያስጀመሩት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት […]

በአማራ ብሄራዊ ክልል ትምህርት ቤቶች ላይ የተደረገ ጥናት ተማሪዎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ መማራቸው ውጤታቸው ዝቅ እንዲል አድርጓታል ብሏል፡፡  

የኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ ላይ የቀድሞው የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ዶ/ር ቴውድሮስ አድሃኖም ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የህፃናት ማቆያ ምእከል ግንባታ ቢጀመርም አሁንም እናቶች ልጆቻቸውን ወደ ስራ ቦታ ይዘው መጥተው በነፃነት ስራቸውን መስራት አልቻሉም ሲሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስተር የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላምሮት ተናግረዋል፡፡ በኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት […]

የኢትዩጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቡርት ማልት ለተባለ የቢራ ብቅል አብቃይ ድርጅት የ15 ሄክታር የመሬት ሊዝ አስረክቧል፡፡ ድርጅቱ 60ሜትሪክ ቶን የቢራ ብቅል የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ የመገንባት እቅድ ሲኖረው ቦታው የተሰጠውም በደብረብርሀን ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ነው፡፡ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከድርጅቱ ጋር የተፈራረመው እና ሊዙንም ያስረከበው ባሳለፍነው አርብ ሲሆን የኢንቨስትመንት ኮሚሽኑ በዚህ አይነት የግብርና ምርት በማቀነባበር ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን […]

የትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሰባተኛ መገጣጠሚያ ማሻሻያ ስራዉን አስመረቀ፡፡ የብለንበርግ ግሎባል ሮድ ሴፊቲ ኢንሼቲቭ ከተባለዉ ግብረ ሰናይ ድርጅትና አጋር ድርጅት ከሆነዉ ናክቶ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የሚታየዉን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ፤ የመንገድ ተጠቃሚዉ የትራፊክ ስርዐትን እንዲከተል ማድረግ በከተማዋ መንገዶች ላይ ማሻሻያዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መንገዶች መካከል ብዙ እንቅስቃሴ የሚደርግበት የሰባተኛ አካባቢ የመንገድ መገጣጠሚያ ማሻሻያዉን አስመርቋል፡፡ […]

አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በ2009 የአስረኛ ክፍልን ለተፈተኑ የሁለት ክልሎች ተማሪዎች እስካሁን ውጤት አለመስጠቱ ታወቀ፡፡ አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በህግ በተሰጠው ተልዕኮ መሰረት የትምህርት ማህበረሰቡን እርካታ ከፍ የሚያደርጉ አገልግሎቶች እንዲሰጥ ቢጠበቁበትም ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ በ2009 የአስረኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱት ውስጥ የሁለት ክልሎች ተማሪዎች ውጤት በኤጀንሲው አልተሰጣቸው ፡፡ የኢፌድሪ […]

በሃገሪቷ በሚገኙ ኢንደስተሪ ፓርኮች የመሰረተ ልማት ችግር እንዳለ ተገለፀ፡፡ የኢንደስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን 2010 ነበጀት አመት አቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የሩብ አመት አፈፃፀም ላይ ፣በቋሚው ኮሚቴው ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ለሴቶች ና ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚነት አንፃር ወጣቶች መቶ በመቶ ተጠቃሚ ሲሆኑ ሴቶች ግን ከ95 በመቶ በላይ በእነዚህ ኢንደስተሪ ፓርኮች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ኢንደስተሪ ፓርኮችን ለመገንባት የተለያዩ ቦታዎችን በተመለከተ […]


[There are no radio stations in the database]