Author: zami zami

Page: 2

ሀገሪቱ ከገባችበት  አለመረጋጋት ለመውጣት አርቆ አሳቢነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የኢትዮጲያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂዎች በወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ በሰጡት ጋዜጣ መግለጫ  በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩትን አለመረጋጋቶች ለመፍታት አርቆ አሳቢነት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአገሪቱ በተለይም ከፍተኛ የትመህርት ተቃማት በሚገኙባቸው አካባቢዎች በአገሪቱ ልማትና እድገት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ወጣት ተማሪዎች ተጠቃሚ አልሆኑም ፡፡ የወጣቶቹን ተጠቃሚ አለመሆን ተከትሎና […]

ህጋዊ ፍቃድ ሳያገኙ ስልጠና በሚሰጡ የትምህርት ማሰልጠኛዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነዉ፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ትክክለኛ የሆነ ህጋዊ ፍቃድ ሳያገኙና ያልተገባ የትምህርት ክፍያ በሚጠይቁ የግልና የክረምት ስልጠና በሚሰጡ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡ ከዚህ ቀደም ሲል የበጋዉን ወራት በትምህርት አሳልፈዉ በክረምት ወራት የማጠናከሪያ ትምህርት ለሚወስዱ ተማሪዎች ክረምቱን አልፎ በመደበኛ የትምህርት ጊዜ ትምህርት […]

በኢትዮጵያ የካንሰር ሀኪሞች ማነስ ህክምናውን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ከበሽታው ድብቅ ባህሪይ የተነሳም ብዙ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት አይደለም። በሽታውን ለመከላከልም ሆነ ለማከም ያለውን እንቅስቃሴ እንኳን ብናይ በሀገራችን የካንሰር ህክምና እየተሰጠ ያለው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል ብቻ ነው። በሀገራችን ስላለው የበሽታው ስርጭትም ቢሆን በቂ የሆነ መረጃ እጥረት መኖሩን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያ ደግሞ ከታዳጊ ሀገራት […]

እንቦጭ አረም ያደረሰውን ጉዳት የሚመረምር የጋዜጠኞች ቡድን ወደ ባህርዳር ሊጓዝ ነው፡፡ ከተለመደው ሙያዊ ሃላፊነት ባለፈ ዜግነታዊ እና ሃገራዊ ግዴታውን ለመወጣት የተቋቋመው የኢትዮጲያ በጎ ፈቃደኛ ጋዜጠኞች ኔትወርክ ተቋቁሟል፡፡ ኔትወርኩ የጣና ሀይቅን በመውረር በሃይቁ ላይና ሃይቁ ውስጥ ኑሯቸውን ባደረጉ እንስሳት ላይ ያደረሰውን መጠነ ሰፊ ጉዳት ከስፍራው ላይ በመገኘት በችግሩ ዙሪያ ሰፊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ለማቀረብ ነው፡፡ የኔትወርኩ አስተባባሪ […]

  የሶማሌ ክልል ፕ/ት አቶ አብዲ ኡመር መሃመድ በምእራብ ሃረርጌ በተፈፀመው የጅምላ ግድያ ላይ ለዛሚ ሬድዮ የሰጡት ቃለመጠይቅ አንኳር ነጥቦች (ቃል በቃል የተፃፈ አይደለም – ሙሉውን ለማድመጥ የድምፅ ፋይል ከታች ያገኛሉ) እኛ እየተፈጠረ ያለውን የሰማነው ታህሳስ 6 ጠዋት ላይ ነው። ወድያውኑም ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ጀምሮ የመከላከያ እና የኢህአዴግ አመራር እንዲያውቁ አድርገናል። መከላከያ ከቦታው የ80 ኪ.ሜ […]

ቆይታ ከሚሚ ስብሃቱ ጋር ፡- በባለፈው ሳምንት ውይይት የኢዴፓ ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ አዳነ ታደሰ ከድርድሩ ለመገለላቸው ምርጫ ቦርድ እጁ እንዳለበት ገልፀው የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የምርጫ ቦርድ ዋና ሃላፊ አቶ ነጋ ዱንፊሳ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

፡ ክልሎቹ ትግራይ፤ጋምቤላ፤ሀረር፤ የኢትዩጲያ ሶማሌ እና አፋር ናቸው፡፡የኢትዩጲያ ዴሞግራፊክ እና ጤና ሰርቬይ ጥናት እንደሚያሳየው በሀገሪቱ ከሚገኙ ያገቡ ሴቶች 68 በመቶው በባላቸው ድብደባ ይደርስባቸዋል፡፡15683 እድሜያቸው ከ15-49 የሆኑ ሴቶች እና 12688 ወንዶች በተሳተፉበት ጥናት ውጤት መሰረት አሁን ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ጊዜያዊ መጠለያ የሌላቸው ክልሎች ጾታዊ፤ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት ደረጃ ሰፍሯል፡፡ በዚህም በትግራይ ክልል ከሚገኙ ሴቶች 25 […]

ትክክለኛ እድሜዋ አከራካሪ ቢሆንም የደቡብ አፍሪካ ተመራማሪዎች የ3.7 ሚሊዮን ዓመት እድሜ ባለፀጋ መሆኗን ተናግረዋል። ይህ ማለት ደግሞ ከኢትዮጵያዊቷ ሉሲ ባለትንሽ እግሯ ሰው ከ500,000 ዓመት በፊት ኖራለች ማለት ነው። ተመራማሪዎች በአፍሪካ የሰው ዘር መገኛ ከዚህ ቀደም ከሚታሰበው በተለየ ቦታ ተበትነው እንደሚገኙ ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ዝርያዎች መኖራቸውንም ያመለክታል። ባለትንሽ እግሯ በሰሜን ምእራብ ደቡብ አፍሪካ ስትርክፎንቴይን […]

በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተለያዩ የስራ ቦታዎች ላይ የሚገኙ አሁንም ራሳችሁን አጋልጡ እየተባሉ ነው፡፡ በዚህ ሂደትም በየክልሉ እራሳቸውን ያጋለጡ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተጠቅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ቁጥር እርግጠኛ ሆኖ የተቀመጠ ቁጥር ባይኖርም በአማራ ክልል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጋለጥ በተሰጠው የአንድ ወር ጊዜ ከሦስት ሺህ በላይ ጥቆማዎች ለክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብል ልማት ቢሮ ደርሶታል ፡፡ በኦሮሚያ […]

የባርነት ንግድ እየተካሄደባት በምትገኘው ሊቢያ ኢትዮጲያ ዜጎቿን መሰብሰብ አዳጋች ሆኖባታል::


[There are no radio stations in the database]